

Application description
Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ on PCGeez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ, coming from the developer ብራና አፕስ Birana Apps, is running on Android systerm in the past. No more eyeing the battery or frustrating calls at the wrong time any more.Just enjoy Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ PC on the large screen for free!Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ Introductionበይዘቱ ተሟልቶ በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ) የተዘጋጀ የመጀመሪያው ምሉዕ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ደንብ ጠብቆ የተዘጋጀ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንዲሁም የቀኖና መጻሕፍት ብላ በ1962 ዓ.ም ያሳተመችውን መጽሐፍ ቃል በቃል ለቅሞ መዝግቧል።መጽሐፉ ለሃይማኖት አባቶች ለሰባክያነ ወንጌልና ለመምህራን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ በሚሰማሩበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ በእጃቸው መያዝ ሳይኖርባቸው በቀላሉ ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማር ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል:: ምዕመናንም የግዕዙንና የአማርኛውን ትርጉም ምሥጢሩ ሳይዛባ በስልካቸው እንዲጠቀሙ ይረዳል::የመጽሐፉ ልዩ ባሕርያት• ሰማንያ አንድ (81) መጻሕፍትን ያካተተ ነው።• ሙሉ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ቋንቋ በግዕዝ፣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ ነው።• የአማርኛው ትርጉም በጥንታዊው የአባቶቻችን አጻጻፍና አገላለጽ ሃይማኖታዊ ለዛውን ሳይለቅ የተጻፈ ነው።• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸውን የብሉይና የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍትን ያካተተ ነው።• ፊደሉና አጻጻፉ በግእዝና በአማርኛ መዛግብተ ቃላት መሠረት ታርሞ የተዘጋጀ ነው።• የፊደሎችን መጠን በቀላሉ ማስተካከያ መንገድ አለው።• በቀንና በጨልማ ለማንበብ የራሱ ማስተካከያ ተካቶበታል።• ማስታወሻ መያዣ፣ ማቅለሚያ፣ ዕልባት ማድረጊያ ተካቶበታል።• ማጣቀሻዎች በየቁጥሩ የተካተቱ ሲሆን በቀላሉ አንድ ጊዜ ብቻ ጠቅ በማድረግ ገጹን ሳይለቁ ማንበብ ያስችላል።• በጣም ፈጣንና የፍለጋ ውጤቶችን በማቅለምና በቁጥር የሚያሳይ መፈለጊያ ተካቶበታል።• የአማርኛ፣ የግእዝና የእንግሊዝኛ ዕትሞችን ጎን ለጎን፣ መስመር በመስመር ፣ ከላይና ከታች አድርገን ለማንበብ ያስችላል።• የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በአኅጽሮት ወይም በሙሉ ስም ለመዘርዘር ማስተካከያ ተደርጎበታል።• የፊደል መጠኑን በቀላሉ ማሳነስና ማሳደግ የሚያስችል ማስተካከያ ተካቶበታል።• የመጽሐፍ ቅዱስ መስመሮችን እንድፍላጎትዎ ማስተካከል ይችላሉ።• ከዚህ በፊት ያነበቧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከዚህ በፊት የተነበቡ በሚለው ስር ያገኟቸዋል።• የተለያዩ ቋንቋዎችን በመጠቀም የመጽሐፉን ይዘት መተርጎም ይችላሉ።ከ66ቱ መጻሕፍት በተጨማሪ 19 የብሉይ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት እና 8 የአዲስ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍትን በግእዝና በአማርኛ አሟልቶ ተዘጋጅቷል ። የብሉይ ኪዳን ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት1. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል2. መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ3. መጽሐፈ ጦቢት4. መጽሐፈ ዮዲት5. መጽሐፈ አስቴር6. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ፣ ካልእና ሣልስ9. መጽሐፈ ሲራክ10. ጸሎተ ምናሴ11. ተረፈ ኤርሚያስ12. ሶስና13. መጽሐፈ ባሮክ14. መጽሐፈ ጥበብ15. መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ16. ተረፈ ዳንኤል17. መጽሐፈ ኩፋሌ18. መጽሐፈ ሔኖክ19. መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት⒈ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ⒉ መጽሐፈ አብጥሊስ⒊ ግጽው ዘሲኖዶስ⒋ ሥርዓተ ጽዮን⒌ መጽሐፈ ዲድስቅልያ⒍ መጽሐፈ ትእዛዝ⒎ መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ እና ካልእያውርዱና ብዙ የተደከመበትን መጽሐፍ ቅዱስ በእጅዎ ያስገቡ።
Read
more
Read
less
Developer Company
Other Details
Other Tags: Books-&
Technical Specs
System Requirement: OS: Windows 8.1 64-bit or Windows 10 64-bit, GPU: GTX 1050, CPU: i3-8300, Memory: 8GB RAM, Storage: 1GB available space